የተከበራችሁ የኮሌጃችን አመራሮች፤

የተከበራችሁ የኮሌጃችን አመራሮች፤

ዲጂታል አማራ (Digital Amhara) ስትራቴጂን በተቋማችን ውስጥ ለማስረጽ በምናደርገው ጥረት፣ ቀደም ሲል ለኮሌጁ የአስተዳደር ሰራተኞችና ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠታችንና ውጤታማ ስራ መከናወኑ ይታወሳል።

ይህንን የጀመርነውን ስኬታማ ጉዞ ይበልጥ ለማስፋትና ስትራቴጂውን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ አሁን ደግሞ፦

🔹 ለአሰልጣኞችና ለሰልጣኞች፣
🔹 ለዞን፣ ለወረዳና ለከተማ አስተዳደር የሥራና ስልጠና አመራሮችና ባለሙያዎች፣
🔹 እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ፣
ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መፍጠር የግድ ይላል። ይህንን ትልቅ አገራዊና ክልላዊ ፋይዳ ያለው ስራ ለማሳካት የእናንተ የአመራር ድጋፍና የመድረክ ዝግጅት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ፣
ሁሉንም ባለድርሻ አካላትና ማህበረሰቡን የሚያገናኝ መድረክ እንድታመቻቹልን ጥሪያችንን እናቀርባለን።

አላማችን፡

✅ የጀመርነውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ወደ ሁሉም ተደራሽ ማድረግ።
✅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የተቀናጀ አሰራርና የነቃ ማህበረሰብ መፍጠር።
✅ በክልልና በዞን ደረጃ ለሚፈለገው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዝግጁ መሆን።

“የአመራሩ ቁርጠኝነት ለዲጂታል አማራ ስኬትና ለማህበረሰቡ ተጠቃሚነት የጀርባ አጥንት ነው!”

📩 የዲጂታል አማራ ፎካል ፐርሰን

Comments

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *