EN አማ
Back to News
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአረብ ሃገር ተመላሽ፣ ለካንፖኒዎች ስልጠናዎችን

ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአረብ ሃገር ተመላሽ፣ ለካንፖኒዎች ስልጠናዎችን

Sintayehu  |  November 6, 2026 at 7:17 AM  |  16 days ago  |  50 views


ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለአረብ ሀገር ተመላሽ ዜጎች ፣ ለአምራች እና አገልግሎት ሰጪ ኢንዱስትሪዎች ከ EDI ጋር በመተባበር የስራ ማስጀመሪያ እና የካንፓኒ ውስጥ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።


‎​ይህ ስልጠና ማህበረሰቡን በኢኮኖሚ ከማጠናከር ባለፈ ሰራተኞች ተቀጥረው በሚሰሩበት ድርጅት አቅማቸውን እና ሙያቸውን እንዲያዳብሩ፣ ተመላሽ ዜጎች ደግሞ በሀገራቸው ውስጥ በራስ መተማመናቸውን በመጨመር የራሳቸውን የንግድ ስራ ፈጥረው ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።
⭐️ ‎​የ‎​ስልጠናው ‎​ተሳታፊዎች በስራ ዓለም ውጤታማ እንዲሆኑ እና ጠንካራ መሠረት እንዲጥሉ በስልጠና ርዕሶች ላይ ሰፊ ትኩረት ተሰጦባቸዋል፦
➤ ‎በስልጠናው የተገኙ ከአምራች አኢንዱስትሪዎች 
ወ 48 ሴ 35=ድ 83ስሆኑ
➤የአረብ ሀገር ተመላሾች በአጠቃላይ ወንድ 16 ሴት 2 10ድምር 226 በስልጠናው እየተሳተፉ ይገኛል።
➤የሆቴል አኢንዱስትሪ ሰራተኞች እና  የህከምና ባለሙያዎች ስልጠና ተሳታፊዎች 
ወ 16 ሴ 20 ድ 36 
ስልጠናው በ Kaizen, Enterepreneurship/ marketing/, productivity Improvement, Safety, work Ethics,  packing & Branding, Quality assurance በሚሉ በተመረጡ  ርዕሶች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
‌‎​በስልጠናዉ ወቅት ሰልጣኞች እንደተናገሩት፦
‎​የዚህ ዓይነት ስልጠናዎች መዘጋጀታቸው  እኛ ከስነ-ልቦናዊ ጫና እንድንወጣ ብቻ ሳይሆን፣ ያለንን እውቀትና አቅም አዳብረን በሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ውስጥ ንቁ ተሳታፊ እንድንሆን ያደርገናል። ክትትል እና የፋይናንስ ድጋፍ ማመቻቸቱ ተጠናክሮ ቢቀጥል ለስኬታችን ዋስትና ይሆናል በማለት አስተያየት ሰጥተዋል።

Previous | Next