EN አማ
Back to News
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018ዓ.ም የስራ አፈፃፀም አንደኛ ደረጃን ያዘ

ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018ዓ.ም የስራ አፈፃፀም አንደኛ ደረጃን ያዘ

Sintayehu  |  September 17, 2026 at 4:48 PM  |  3 days ago  |  10 views

🏆🏆🏆🏆🏆🥇🥇🥇🥇🥇
ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018ዓ.ም በጀት አመት በአጠቃላይ ስራ አፈፃፀም ከም/ጎጃም ዞን በስራ እና ክህሎት መምሪያ ስር ካሉ ኮሌጆች 🥇አንደኛ በመውጣት የሰርተፍኬት እና የዋንጫ ተሸላሚ መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

መስከረም 7/2019ዓ.ም የህ/ግንኙነት ቡድን

ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018ዓ.ም የስራ ዘመን በስራ አፈፃፀሙ የላቀ ውጤት በማስመዝገቡ ከም/ጎጃም ዞን ስራ እና ክህሎት መመሪያ ከሚመሩ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች አንደኛ ደረጃን በመያዝ የዋንጫ እና የሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆን ችሏል።
በኢ/ኤ/አ/ድ/ቡድን የስራ ሂደት አንደኛ 🥇 ደረጃን የያዘ ሲሆን በትም/ስልጠና  የስራ ሂደት ሁለተኛ 🥈ደረጃን ይዟል። በአጠቃላይ የተቋሙ የስራ እንቅስቃሴ አፈፃፀም ከሁሉም ኮሌጆች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ አንደኛ🥇 ደረጃን ይዟል።
👉ለዚህ የላቀ ውጤት መሳካት ከልብ በመነጨ የስራ ተነሳሽነት እና ትጋት የተሰጣችሁን ኋላፊነት በመወጣትና በጥንካሬ በመስራት የጋራ ውጤት ላስመዘገባችሁ አመራሮች 🙏አሰልጣኝ መምህራኖች 🙏 አስተዳደር ሰራተኞች🙏 በአጠቃላይ የኮሌጁ ማህበረሰቦች🙏ከፍተኛ ምስጋና ይገባችኋል!!!
እንኳን ደስ አላችሁ !!!🥇🥇🏆🏆

ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Previous | Next