EN አማ
Back to News
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ አንተነህ ባህሩ ያስተላለፉት የእንኳን

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ አንተነህ ባህሩ ያስተላለፉት የእንኳን

Sintayehu  |  September 11, 2026 at 5:21 PM  |  9 days ago  |  11 views

🇪🇹🇪🇹🇪🇹መልካም አዲስ ዓመት!! 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
                🌼🌼2019ዓ.ም🌼🌼
ከፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን "አቶ አንተነህ ባህሩ" የተላለፈ የአዲስ ዓመት ምኞት መግለጫ፣

ለሁሉም የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች እና ኢትዮዽያውያን ውድ ባልደረቦቻችን፣ በኮሌጁ አስተዳደር ስም እና በራሴ ስም፣ እንኳን ለአዲስ ዓመት 2019 ዓ.ም. በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ።
ያለፈውን ዓመት ስናስብ እና አዲሱን ዓመት ስንቀበል፣ ለፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተልእኮና ራዕይ ያላችሁን /ያለንን ቁርጠኝነት፣ ጠንካራ ስራ እና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት የምናደርገውን ጥረት በጥልቅ አድናቆት እገልጻለሁ። በማስተማር፣ በስልጠና፣ በቴክኖሎጂ፣ ኢንዱስትሪ አኤክስቴንሽን ድጋፍ፣ በአስተዳደር እና በድጋፍ አገልግሎቶች የምታደርጉት /የምናደርገው ያልታከተ ጥረት የተቋማችን እድገትና ስኬት መሠረት ሆኗል።
አዲሱ ዓመት 2019 ዓ.ም. ለእናንተ እና ለቤተሰቦቻችሁ ብዙ ጤና፣ ደስታ፣ ሰላም እና ብልጽግናን ይሁንልን። አዲስ ኃይል፣ ሙያዊ እድገት፣ ጠንካራ የቡድን ስራ እና ለኮሌጃችን ታላላቅ ስኬቶች የምናሳካበት ዓመት ይሁንልን። አንድነት፣ ፈጠራ እና ልህቀት በመያዝ በጋራ በመስራት ለማህበረሰባችን እና ለአገራችን ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ብቁ ምሩቃንን ማፍራታችንን እንቀጥል።ለመላው ኢትዮዽያውያን
መልካም እና በረከት የተሞላ አዲስ ዓመት እመኛለሁ!
ከሰላምታ ጋር፣ አንተነህ ባህሩ ዋና ዲን ፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Previous | Next