EN አማ
Back to News
በ22/11/2018 ዓ.ም በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ በፍኖተ ሰላም ከተማ የሴፍቲኔት አባላትና ባለሙያዎች ከኮሌጁ ሰራተኞች ጋር በመቀናጀት የተሻሻሉ የማንጎ ተክሎችን የመትከል ስራ በስኬት ጀምረዋል። ይህ የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን የመትከል እንቅስቃሴ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

Sintayehu  |  July 29, 2026 at 7:26 AM  |  1 month ago  |  38 views

በ22/11/2018 ዓ.ም በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ በፍኖተ ሰላም ከተማ የሴፍቲኔት አባላትና ባለሙያዎች ከኮሌጁ ሰራተኞች ጋር በመቀናጀት የተሻሻሉ የማንጎ ተክሎችን የመትከል ስራ በስኬት ጀምረዋል። ይህ የአትክልትና ፍራፍሬ ተክሎችን የመትከል እንቅስቃሴ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።

የኮሌጁ የትምህርትና ስልጠና ምክትል ዲን አቶ ቸኮል አየለ እንደገለጹት፤ የዚህ ስራ ዋና ዓላማ የኮሌጁን ግቢ ምቹና ማራኪ ከማድረግ ባለፈ፣ በሚበሉና የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ በሚችሉ ተክሎች ተቋሙን መሸፈን መሆኑን አስገንዝበዋል።

በተጨማሪም የፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር የሴፍቲኔት ባለሙያ አቶ ተስፋዬ ሞላ፤ ተቋሙ ለተጠቃሚዎች በሰጠው ቦታ ላይ አትክልትና ፍራፍሬ መትከል ዋነኛ ግዴታቸው መሆኑን ጠቅሰው፣ ስራው ውጤታማና ዘላቂ ይሆን ዘንድ ከኮሌጁ ጋር በጋራና በምክክር መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

Previous | Next