EN አማ
Back to News
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 110 ተማሪዎችን አስመረቀ፤

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 110 ተማሪዎችን አስመረቀ፤

Sintayehu  |  July 18, 2026 at 4:52 PM  |  2 days ago  |  6 views

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 110 ተማሪዎችን አስመረቀ፤
****
ፍኖተሰላም፡ ሐምሌ 11/2018ዓ.ም (ኮሙዩኒኬሽን)

በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ አስተዳደር የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ14ኛ ዙር ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ 5 በቀን የትምህርት መርሃ-ግብር በአምስት የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ወንድ 39፣ ሴት 71፣ በድምሩ 110 ተማሪዎች በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት አስመረቀ።

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አንተነህ ባህሩ ተመራቂ ተማሪዎች በቆይታቸው ያሳዩትን ጥንካሬ በማድንቅ ቀጣዩ ህይወታቸው በማንኛውም ቦታ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ  መልካም ምኞታቸው ገልፀዋል።

የሀገርን እድገት ለማረጋገጥና ለማፋጠን ቴክኖሎጅን በላቀ ብቃት ለመጠቀም የተማረ የሰው ሀይል ያስፈልጋል ፤በዚህም ኮሌጃችን የጥራት ደረጃውን በማሳደግ አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ኮሌጅ እንዲሆን ኮሌጁ የትምርት ተቋም አስተዳደር ስርአትን ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል ብለዋል።

ዲኑ አክለውም ሰልጣኞቹ የሰለጠኑት ሙያም ከሀገር አቀፍ አልፎ በአለም አቀፍ ተወዳዳሪ አንደሚያደርጋቸውና ተማሪዎች በየትኛውም ቦታ ቢወዳደሩ አሸናፊ እንደሚሆኑ ጨምረው ገልፀዋል።

የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ በአምስት የተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተማሪዎችን አሰልጥኖ በማስመረቅ ለከተማዋና ለአካባቢው ልማት አዲስ አቅም እየፈጠረ የሚገኝ ኮሌጅ ነው ብለዋል የኮሌጁ ዲን።

​የፍኖተ ዳሞት የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ባስመረቀበት ደማቅ ሥነ-ሥርዓት ላይ የተገኙት የምዕራብ ጎጃም ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አያልሰው ሙሉ በበኩላቸው ለተመራቂዎች፣ ለወላጆችና ለኮሌጁ ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሐምሌ11/2018ዓ.ም

Previous | Next