EN አማ
Back to News
በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ የተከናወነው የእርሻ ስራ ከአምናው በተሻለና እጅግ በተደራጀ አግባብ በመመራቱ፣ በአሁኑ ወቅት በማሳችን ላይ ተስፋ ሰጪና እጅግ ያማረ ቡቃያ በቅሎ ለማየት በቅተናል።

በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ የተከናወነው የእርሻ ስራ ከአምናው በተሻለና እጅግ በተደራጀ አግባብ በመመራቱ፣ በአሁኑ ወቅት በማሳችን ላይ ተስፋ ሰጪና እጅግ ያማረ ቡቃያ በቅሎ ለማየት በቅተናል።

Sintayehu  |  July 16, 2026 at 6:16 PM  |  4 days ago  |  5 views

በፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዘንድሮ የተከናወነው የእርሻ ስራ ከአምናው በተሻለና እጅግ በተደራጀ አግባብ በመመራቱ፣ በአሁኑ ወቅት በማሳችን ላይ ተስፋ ሰጪና እጅግ ያማረ ቡቃያ በቅሎ ለማየት በቅተናል። ይህ ስኬታማ ጅማሮ የኮሌጃችንን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና ወደፊት የሚገጥሙንን የኢኮኖሚ ፈተናዎች ለመቋቋም የተነደፈውን አቅጣጫ በተግባር ያሳየ ሲሆን፣ በጋራ ከሰራን ልማትንና እራስን መቻልን ማምጣት እንደምንችል ትልቅ ማሳያ ሆኗል።

ለዚህ እፁብ ድንቅ ውጤት መገኘት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በትጋትና በቁርጠኝነት ለሰሩት ለእርሻ ኮሚቴው ፊታውራሪ ለአቶ አበበ እና ብርቱ ባልደረቦቻቸው ደጉ፣ ጥላሁን፣ ሙላት፣ ገረመው፣ ስዮም እንዲሁም ለስራ አስፈጻሚዋ አበባ የላቀ ምስጋናና አክብሮት ይገባቸዋል። የነገውን የኑሮ ውድነት ማስታገሻችንንና ዋስትናችንን በገዛ እጃችን እየገነባን በመሆኑ፣ “በርቱ፣ እንበርታ!” እያልን የጀመራችሁትን አኩሪ ተግባር ይበልጥ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

Previous | Next