EN አማ
Back to News
የፍኖተ ዳሞት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዲጂታል አማራን ፕሮጀክት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ዝርዝር ግምገማ አካሂዷል

የፍኖተ ዳሞት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዲጂታል አማራን ፕሮጀክት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ዝርዝር ግምገማ አካሂዷል

System Administrator  |  July 2, 2026 at 11:14 AM  |  19 days ago  |  20 views

በቀን 25/10/2018 ዓ.ም የፍኖተ ዳሞት ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የዲጂታል አማራን ፕሮጀክት አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ዝርዝር ግምገማ አካሂዷል። በግምገማ መድረኩ ላይም በዋናነት እስካሁን ድረስ በተመዘገቡ፣ ስልጠናውን ባጠናቀቁና ብቁ በሆኑ እንዲሁም እስካሁን ስልጠናውን ባልጀመሩ ሰልጣኞች ሪፖርት ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በዚህም መሰረት እስካሁን ባለው ሂደት በአጠቃላይ 975 ሰልጣኞች የተመዘገቡ ሲሆን፥ ከእነዚህም መካከል 590 ያህሉ ስልጠናውን ወስደው ያለፉ መሆናቸው ተረጋግጧል። በአንጻሩ ቀሪዎቹ ተመዝጋቢዎች እስካሁን ድረስ ወደ ስልጠናው እንዳልገቡ በሪፖርቱ የተመለከተ ሲሆን፥ እነዚህን ገና ስልጠና ያልጀመሩ ሰልጣኞች ወደ ስልጠናው አስገብቶ ብቁ ለማድረግ በጋራ መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ዓመት ከኮሌጁ እቅድ አንጻር በሙሉ አቅም መንቀሳቀስ አስፈላጊ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ ይህ ካልሆነ ግን የተቀመጠውን እቅድ ማሳካት እንደማይቻል በውይይቱ ላይ ስጋቶችና ሀሳቦች ተነስተዋል።

በተለይም ስልጠናውን ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ ትምህርት ቤቶችን፣ የመምህራን ኮሌጅን እንዲሁም ሁሉንም የዞን፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር መስሪያ ቤት ሰራተኞችን በስልጠናው ማሳለፍ እንደሚገባ ተገልጿል። ለዚህም ትልቅ ግብ መሳካት የመንግስት አመራሮች አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ሀሳብ ቀርቧል።

Previous | Next