EN አማ
Back to News
የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በዲጂታል አማራ የስልጠና እንቅስቃሴ ላይ ውይይት አካሄደ

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት በዲጂታል አማራ የስልጠና እንቅስቃሴ ላይ ውይይት አካሄደ

Sintayehu  |  May 27, 2026 at 10:26 AM  |  1 month ago  |  47 views

የፍኖተ ዳሞት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ "የድጅታል አማራ" ስልጠና አስተባባሪዎች /ቴክኒካል ኮሚቴዎች/ እና የዘርፍ ተጠሪዎች በተገኙበት አፈፃፀሙን በመገምገም ለቀጣይ የስራ ውጤት በምን መልኩ ማስቀጠል አለብን በማለት ሠፊ ውይይት አደረጉ።

በውይይቱ ለአፈፃፀሙ መቀነስ መንስኤዎች ተገልፀው ለቀጣይ ማሻሻያ ነጥቦች እና የስራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። 
- በቂ የኢንተርኔት አክሰስ አለማግኜት ፣ ስራውን ለICT ዘርፍ ብቻ መተው፣ ተመዝጋቢው ትኩረት ሰጥቶ ወደ ስልጠናው አለመግባቱ እና የአመራሮች ክትትልና ድጋፍ አናሳ መሆኑ አፈፃፀሙ ሊወርድ እንደቻለ በውይይቱ የተገለፀ የጋራ ሃሳብ ሲሆን፦ በቀሪ ቀናቶች ሁሉም የቴክኒካል ኮሚቴዎች እና የዘርፍ ተጠሪዎች ትኩረት ሰጥተው የተሻለ የድጅታል አማራ ሰልጣኝ ተመዝጋቢ ብቻ ሳይሆን በመሰልጠን ሰርተፍኬት እንዲያገኙ ማድረግና መደገፍ እንደሚገባ ፣የኢንተርኔት አገልግሎቱን ችግር data  በመሙላት የሚቀረፍ መሆኑን እና አመራሮችም በቅርበት ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ በመግለፅ እንደኮሌጅ በርብርብ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንደሚገባ "አቶ ቸኮል አየለ" /የኮሌጁ ም/ዲን/ የተገለፁ ሲሆን ቤቱም በተሰጠው ሀሳብ  ተስማምቶ ለተሻለ የስራ አፈፃፀም እንሰራለን በማለት ውይይቱ ተቋጭቷል ።


19/09/2018ዓ.ም
ፍ/ዳ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ

Previous | Next