EN አማ
Back to News
የተከበራችሁ የኮሌጃችን ማህበረሰብ አባላት በሙሉ

የተከበራችሁ የኮሌጃችን ማህበረሰብ አባላት በሙሉ

Sentayehu  |  May 26, 2026 at 11:08 AM  |  1 month ago  |  40 views

የተከበራችሁ የኮሌጃችን ማህበረሰብ አባላት በሙሉ፣ የኮሌጃችንን ገጽታ በዲጂታል ዓለም ለማስተዋወቅና ተደራሽነታችንን ለማሳደግ ታቅዶ የተገነባው የኮሌጃችን ኦፊሴላዊ ድረ-ገጽ (https://fdcollege.edu.et) ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል። ይህ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤት የኮሌጃችንን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች፣ የትምህርት አሰጣጥ ሂደቶች እና የልህቀት ጉዞዎች በይፋ የምናንፀባርቅበት ዋነኛ መድረክ ይሆናል።

ይህ ድረ-ገጽ የኮሌጃችንን ዓላማ በአግባቡ እንዲያገለግል፣ በየክፍሉ የሚከናወኑ አጫጭር ዘገባዎች፣ አዳዲስ ማስታወቂያዎች፣ መርሃ-ግብሮችና የተለያዩ ኩነቶች (Events) በወቅቱ መለጠፍ ይኖርባቸዋል። ለዚህም እንዲያመች፣ ማንኛውም መረጃ ለማሰራጨት የሚፈልግ የክፍል ኃላፊ ወይም የሥራ ክፍል፣ መረጃዎቹን በኮሌጃችን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ በኩል በማስተላለፍ እንዲያስለጥፍ ጥሪ እናቀርባለን።

በመሆኑም የትምህርት ክፍሎቻችሁና የሥራ ክፍሎቻችሁ የሚሰሩትን አበይት ተግባራት ለህዝብ ግንኙነት ክፍል በመላክ ድረ-ገጻችንን በጋራ እንድናበለጽግና የኮሌጃችንን ገጽታ እንድንገነባ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን። ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ማለትም 100GB ብቻ ስለሆነች ማንኛውም ግለሰብ መረጃ መለጠፍ ለጊዜው ከልክለናል፤ ወደ ፊት ያልተገደበ ሰርቨር ሲኖረን ክፍት እናደርገዋለን።

የላቀ የዲጂታል አገልግሎትን እውን ለማድረግ ላሳያችሁት ትብብር የዲጂታል ኮሚቴው ምስጋናውን ያቀርባል።

Previous | Next